አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ኢትዮሊዝ ኦፕታልሚክ ሰርጂካል ማይክሮስኮፕ ለዋጋ የይን ማዕከል በፋይናንስ ሊዝ አስተላለፈ

ኢትዮሊዝ ኦፕታልሚክ ሰርጂካል ማይክሮስኮፕ ለዋጋ የይን ማዕከል በፋይናንስ ሊዝ አስተላለፈ
ኢትዮሊዝ ኦፕታልሚክ ሰርጂካል ማይክሮስኮፕ ለዋጋ የይን ማዕከል በፋይናንስ ሊዝ አስተላለፈ

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የግል የካፒታል እቃዎች በፋይናንስ ሊዝ አቅራቢ ድርጅት የሆነው ኢትዮሊዝ ዛሬ መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው እጅግ ዘመናዊ ኦፕታልሚክ ማይክሮስኮፕ ለዋጋ (WGGA) የአይን ህክምና ማዕከል የሊዝ ዉሉ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ የእቃውን ባለቤትነት አስተላለፈ፡፡

ይህም ኢትዮሊዝ በሀገር ውስጥ ካሉ የህክምና እና ዳያግኖስቲክ ማዕከሎች ጋር በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዙ የህክመና መሳሪያዎችን በሊዝ ለማስተላለፍ ከገባቸው ስምምነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዛሬ የተላለፈው ማይክሮስኮፕም ዋጋ የአይን ማዕከል አጠቃላይ የአይን ምርመራዎችን፣ እነዲሁም እጅግ የላቀ የአይን ህክምና መስጠት እንዲያስችለው የሚያደርግ ነው፡፡



ኢትዮ ሊዝ በግል ዘረፍ እና በሀገሪቱ ልማት ላይ ማነቆ የሆነውን የካፒታል እቃዎች እጥረት ለመግታት ለጤና እና ለሌሎች ቁልፍ ሚና ላላቸው ዘርፎች በከፍተኛ ቴክኖሎጂ የታገዙ እና ጥራት ያላቸው የህክምና መሳሪያዎችን ከሙሉ ዋስትና እና መለዋወጫ እቃዎች ጋር በማቅረብ እየደገፈ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ሁለት አመታት ኢትዮሊዝ በግብርናው ዘርፍ ያለውን የእርሻ መሳሪያ ፣በጤናው ዘርፍ የህክምና መገልገያዎች እና በማኑፋከቸሪንግ ዘርፍ የሚያስፈልጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከባድ ማሽኖችን እጥረቱን ለመቅረፍ አስመጥቶ በሊዝ ፋይናንስ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡

በርክክብ ስነስረዓቱ ወቅት የኢትዮሊዝ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደጎል ጎሳዬ « ዛሬ ያደረግነው የዚህ እጅግ ዘመናዊ ኦፕታልሚከ ማይክሮስኮፕ ርክክብ ድርጅታችን የግሉን ዘርፍ ለማገዝ የሚያቀርባቸው መፍትሄዎች ማሳያ ነው፡፡»

የዋጋ የአይን ህክምና ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር መላኩ መንግስቱ በበኩላቸው «ከኢትዮሊዝ ጋር በጋራ መስራታችን ስራችንን እንድድናቀላጥፍ ከማገዙም በተጨማሪ ባለን ሀብት ልዩ ስራዎችን እንድንሰራ ረድቶናል፡፡ እንዲህ ያለው አጋርነት በተለይ በእኛ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው እና ሊበረታታ የሚገባው ነው፡፡ ላደረግነው ጥምረትም እጅግ እናመሰግናለን፡፡»

ኢትዮሊዝ ከምስረታው አንስቶ የመገልገያ መሳሪያዎችን እጥረት ለመቅረፍ ለግብርና፣ ለጤና፣ ለሀይል ፣ የምግብ ማቀነባበርያ ዘርፎች እና ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የፋይናንስ ሊዝ አገልግሎትን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስም በጥቅሉ 25 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ያላቸው የሊዝ ስምምነቶችን አድርጓል፡፡



ሙሉ በሙሉ በአፍሪካ አሴት ፋይናንስ ድርጅት ስር የሚተዳደረው ኢትዮ ሊዝ በ2011 ዓ.ም ከብሄራዊ ባንክ ፍቃድ ካገኘ በኋላ ነበር በኢትዮጵያ ስራውን የጀመረው፡፡ በሀገሪቱም ያለውን የመሳሪያ እጥረት እና የውጨ ምንዛሬ ዕጥረትን ለመቅረፍ የተቋቋመ ለተመረጡ እቃዎች ፋይናንስ የሚያደርግ በአይነቱ ልዩ የሆነ ድርጅት ነው፡፡በዚህም ግብርና፣ጤና ፣ሀይል፣ ምግብና ቡና፣ እንዲሁም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን እያገዘ ይገኛል፡፡ ስለ ኢትዮሊዝ የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ፤ እባክዎን ይህን ማስፈንጠርያ ተጭነው ይመልከቱ፡፡ www.ethiolease.com.

ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ እና በኔዘርላንድ ሮተርዳም ያደረገው አፍሪካ አሴት ፋይናንስ ኩባንያ አይነተኛ አማራጮችን በማቅረብ ደንበኞች መሳሪያውን ከመጠቀም ከሚያገኙት የገንዘብ ፍሰት የሚከፍሉበት እንዲሁም እቃን እንደ አገልግሎት መጠቀም እና የካፒታል እቃዎችን ፋይናንስ የማድረግ አገልግሎቶችን በማቅረብ ልምድን ያካበተ አለም አቀፍ ድርጅት ነው፡፡ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ይኸው ኩባንያ በተለያዩ ሀገራት ውስጥም ቢሮዎችን ከፍቶ እየሰራ ይገኘል፡፡

Related Post