አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

አባሀዋ ትሬዲንግ 34 ሚሊዮን ደላር የዉጭ ምናዛሬ አስገኘ

አባሀዋ ትሬዲንግ 34 ሚሊዮን ደላር የዉጭ ምናዛሬ አስገኘ
አባሀዋ ትሬዲንግ 34 ሚሊዮን ደላር የዉጭ ምናዛሬ አስገኘ

አባሃዉ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ2012 አ.ም ከ34 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለዉ ቡና ወደ ዉጭ መላኩን ገለፀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስከያጅ አቶ እንየዉ ዘለቀ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ በተለይ እንደተናገሩት ድርጅቱ ያስገኘዉ የዉጭ ምንዛሬ ባለፈዉ አመት ካስገባዉ በ14 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አምስት አመታት ዉስጥ በአጠቃላይ አባሀዋ ትሬዲንግ ከ150 ሚሊዮን ዶላር በላይ የዉጭ ምንዛሬ ከቡና ንግድ እንዳስገባ አቶ እንየዉ ገልፀዋል፡፡ሰኔ30 በተጠናቀቀዉ የበጀት አመት ኢትዮጵያ ወደ ዉጭ ከተላከ ቡና ከ846 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷን የንግድና ኢንደሰትሪ መረጃ ያሳያል፡፡

ገቢዉ የተገኘዉ አባሀዋን ጨምሮ ወደ 400 የሚጠጉ ቡና ላኪዎች ከላኩት ምርት መሆኑን መረጃዉ ያመለክታል፡፡ አባሃዋ ቡና በመላክ ላለፉት አመታት የተሻለ አፈፃፀም በማሳየቱ ተሸላሚ እንደነበረም አቶ እንየዉ አስታዉቀዋል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=b_988oI6me8[/embedyt]

Related Post