አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

አባሀዋ ትሬዲንግ ለ800 ሰራተኞች የስራ አድል ፈጥሪያለዉ አለ

አባሀዋ ትሬዲንግ ለ800 ሰራተኞች የስራ አድል ፈጥሪያለዉ አለ
አባሀዋ ትሬዲንግ ለ800 ሰራተኞች የስራ አድል ፈጥሪያለዉ አለ

ኩባንያዉ ሲመሰረት ከነበረዉ 80 ሰራተኞች ወደ 800 ቋሚ ሰራተኞች ማሳደጉን የኩባንያዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ እንየዉ ዘለቀ በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ኩባንያዉ በአሁኑ ወቅት ወደ ዉጪ ቡና ከመላኩ በተጨማሪም ዋን የተባለ የታሸገ ዉሃ በማምረት እና በማከፋፈል ስራ ላይ እንደሚገኝ አቶ እንየዉ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በሌሎች ዘርፎች ላይ በመሰመራቱ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የገለፁት ዋና ስራ አስኪያጁ የተጀመሩት የጁስ ማምረቻ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች ማስፋፊያ ከተጠናቀቁ ለተጨማሪ 300 ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

አቶ እንየዉ እንደገለፁት ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ቢፈጥርም ለስራ ማስፋፊያ ለምንፈልገዉ የመሬት አቅርቦ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደርንና ለኦሮሚያ ክልል ጥያቄ ብናቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ አባሃዋ ትጌዲንግ ጊዜያዉ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ1000 በላይ ሰራተኞች የስራ እድል እንደፈጠረ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አባሃዋ ትሬዲንግ ባለፈዉ አመት ወደ ዉጪ ከተላከዉ ቡና 34 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለሀገራችን ማስገኘቱ ይታወቃል፡፡ይህም አሃዝ ድርጅቱ ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ካስገኘዉ ምንዛሬ በ12 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለዉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=WZNbPZD-Hj4[/embedyt]

Related Post