አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

አምዮ ኢንጅነሪግ ለ70 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሪያለሁ አለ

አምዮ ኢንጅነሪግ ለ70 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሪያለሁ አለ
አምዮ ኢንጅነሪግ ለ70 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሪያለሁ አለ

አስራ ስምንት አመት በፊት የመንግስት ሰራተኞች የሆኑት አምስት ጎደኛሞች በአዲስ አበባ ፡አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ አምዮ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና እርሻ መሳሪያዎች ኃ/የተ/ግ/ማህበርን መሰረቱ፡፡

በጊዜዉ መነሻ ሀሳበቸዉ የነበረዉ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚያገለግሉ እቃዎችን ለማምረት ነበር፡፡ከዛም በመቀጠል ወደ እርሻ መሳሪያዎች ማማረት እንደተሸጋገሩ የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አኪያጅ አቶ ኢብራሂም ያሲን ይናገራሉ፡፡ከመቀጠር በግል ስራ ማስኬድ ብዙ መሰናክል እንዳለዉ ከተገነዘቡ በኃላ ከአምስት ጎደኛሞች ሶስቱ ባይቀጥሉም አቶ ኢብራሂም ያሲንና አቶ ሙዘሚል መሃመድ ግን ጠንክረዉ በመስራታቸዉ ዛሬ ለ70 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር እንደቻሉ በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የስራ እድል በመፍጠር ላይ የሚገኘዉ የግሉ ዘርፍ እንደሆነ ይታወቃል፡፡የኢትዮጵያ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን መረጃ እንደሚያመለክተዉ ከሆነ ከ10 ስራዎች ዉስጥ አራቱ እንደ አቶ ኢብራሂምና ጎደኛቸዉ በፈጠሩት ስራ የተገኙ ናቸዉ፡፡

በኢትዮጵያ በየአመቱ ወደ ስራ እድሜ ከሚሸጋገሩ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ዉስጥ አንድ ሚሊዮን ብቻ ስራ እንደሚያገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡መንግስት በሚቀጥሉት አስር አመታት ዉስጥ እስከ 20 ሚሊዮን የስራ እድሎች ለመፍጠር በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆነ በቅርቡ ይፋ አድርጎል፡፡

Related Post