አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

አምዮ ኢንጂነሪግ በሃገር ዉስጥ ትራክተር ለመገጣጠም አቅዷል

በሀገራችን ዉስጥ ትራክተር ለማምረት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ለመገጣጠም የዉጭ ባለሃብት በማፈላለግ ላይ መሆኑን የአምዮ ኢንጂነሪንግ መስራችና ስራ እኪያጅ አቶ ኢብራሂም ያሲን ተናግረዋል፡፡

ለ18 አመታት በኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ እና የእርሻ መሳሪያዎችን የሚገጣጥመዉና የሚያመርተዉ ድርጅት የትራክተር ክፍሎችን ለማምረት እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ለመገጣጠም የዉጭ ባለሃብት በመፈለግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡አቶ ኢብራሂም ያሲን በስራ ባሳለፉት አመታት ድርጅቱ ከባንክ ብር ተበድሮ እንደማያዉቁ አሁን ግን ስራዉን ለማስፋፋት የዉጪ ባለ ሃብት ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸዉን በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ አስታዉቀዋል፡፡

በተጨማሪም ትላልቅ ትራክተሮችንና ከዉጪ ከማስመጣት ሙሉ በሙሉ በሃገር ዉስጥ ለማምረትና እያደገ ያለዉን የእርሻ ኢኮኖሚዉን ማገዝ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ አብዛኛዉ የግብርና ስራ የሚከናወነዉ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ባለ አንስተኛ ማሳ አርሶአደሮች ሲሆን የእነዚህ አርሶ አደሮች ስራ በአብዛኛዉን የሚከናወነዉ በበሬ ጫንቃ ላይ የተደገፈ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ከቅርብ ገዜያት ወዲህ ግን እነዚህን አርሶአደሮች መሬታቸዉን በጋራ በትራክተር በማረስ የተሻለ ምርት ለገበያ እንዲያመርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ይታወቃል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=9GKAkNo3exk[/embedyt]

Related Post