አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ቼክ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

ቼክ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች
ቼክ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

ቼክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና፣ በውሃ ልማት፣ በወጣቶች አቅም ማጎልበትና በጂኦሎጂካል ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ተቀዳሚ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሚስተር ጂሪ ኮዛክ አስታወቁ፡፡

ተቀዳሚ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዛሬ ከገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተናገሩት ቼክ ሪፐብሊክ ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ድጋፍ በዩክሬን ራሺያ ጦርነትና እሱን ተከትሎ በታየው የዋጋ ንረት ምክንያት መስተጓጎል እንዳልገጠመው አስታውሰው፤ ቼክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ባለፈው ዓመት ሀገሪቱ ባዘጋጀችው አዲስ የአፍሪካ ፕሮግራም ዋና ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስርድተዋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ እንደሆነ ገልፀው፤ በተለያዩ የልማት ዘርፎች በተለይም የሙዝ ምርት ልማትን በደቡብ ኢትዮጵያ ለማሳደግ የቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ያደረገውን አስተዋፆ አድንቀዋል፡፡

ሚንስትር ዲኤታዋ የቼክ ሪፐብሊክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የተደረገውን የኢኮኖሚ መሻሻያ ተጠቅመው በተለያዩ ዘርፎች ማዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ውጤታማ እንደሚሆኑ አመልክተዋል፡፡

Related Post