አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትን ጠቅሶ የዘገበው የቤተክርስትያኗ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ነው።

ቅዱስነታቸው ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱ ይታወሳል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነሐሴ 29 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ተብለው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት 34 አመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል።

ብጹዕ ወቅ አቡነ መርቆሬዎስ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት የሆኑትን አቋቋም፣ ድጓና ዝማሬ መዋስዕት በላቀ ሁኔታ የተማሩ መሆናቸውን ከሕይወት ታሪካቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Related Post