አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ቡና ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ ሽልማት አበረከተ

ቡና ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ ሽልማት አበረከተ
ቡና ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ ሽልማት አበረከተ

ቡና ባንክ በህዝብ እና የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያዘጋጀዉን 7ኛ ዙር የቁጠባ እና ሽልማት መርሃ-ግብር በማጠናቀቅ የሎተሪ ዕጣ አሸናፊ ቁጥሮችን መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በሕዝብ ፊት የፋ አደረገ፡፡

በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የቁጠባ ባህላቸዉን እንዲያሳድጉ ጥረት ዕያደረገ የሚገኘዉ ቡና ባንክ በህዝብ እና የጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያዘጋጀዉን 7ኛ ዙር የቁጠባ እና ሽልማት መርሃ-ግብር በማጠናቀቅ የሎተሪ ዕጣ አሸናፊ ቁጥሮችን መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በሕዝብ ፊት ያወጣ ሲሆን፣ የሽልማቱ አሸናፊ ደንበኞችም በይፋ ታዉቀዋል፡፡

በዚሁ ስነ ስርሰዓት መሰረትም የዘመናዊ የቤት አዉቶሞቢል አሸናፊ የሎተሪ ዕጣ ቁጥር 4160417 በመሆን ወጥቷል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ተዘጋጅተዉ የነበሩት ሽልማቶች አንድ የቤት አዉቶሞቢል፣ አንድ ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪ፣ አራት የልብስ ማጠብያ ማሽኖች፣ አራት ዘመናዊ ማቀዝቀዣዎች፣ አራት 55 ኢንች ቴሌቪዢኖች፣ አሰራት የዉሃ ማጣርያዎች እና አስር እስማርት የሞባይል ስልኮች ተሸላሚ የሆኑ 28 ባለ ዕድለኛ ደንበኞች በይፋ ዕጣ አወጣጥ ስነ ሥርዓቱ የታወቁ ሲሆን ሽልማቱም በቅርቡ በሚካሄድ ስነ ሥርዓት ለባለ ዕድለኞቹ እንዲደርስ ይደረጋል ሲል ባንኩ በሰጠዉ ጋዚጣዊ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

ባንኩ ቀደም ሲል በመደበኛ ታክሲ፣ ሜትር ታክሲና ባጃጅ ሾፌሮች እና ባለ ንብረቶች ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረዉን በተከታታይ በስድስት ዙሮች ሲያካሄድ የቆየዉን የይቆጥቡ ይሸለሙ መርኃ-ግብር በማስፋት ወደ ፈሳሽና ደረቅ ጭነቶች ማመላለሻ እንዲሁም አነስተኛ መካከለኛና ከፍተኛ የሕዝብ ትራንስፖርት ዘርፍን በማካተት ያሳደገዉ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለ ንብረቶችን፣ አሽከርካሪዎችን እና ረዳቶችን ያካተተ የቁጠባ መርሃ-ግብር በመዘርጋት የተሳታፊዎችን ቁጥር ከፍ ማድረግ እንደተቻለም ጨምሮ ገልጧል፡፡

ባንኩ አሁን ያወጣዉን ዕጣ ለባለ ዕድለኞች የማድረስ ስነ ሥርዓት ካጠጠናቀቀ በኋላ በተመሳሳይ በርካቶችን ተሸላሚ የሚያደርገዉን የመርሃ-ግብሩን 8ኛ ዙር የይቆጥቡ ይሸለሙ ፕሮግራም በይፋ እንደ ሚጀምር አሳዉቋል፡፡

Related Post