አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በ24 ሰዓት ውስጥ 85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

በ24 ሰዓት ውስጥ 85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
በ24 ሰዓት ውስጥ 85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,257 ደርሷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) ደርሷል፡፡::በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስምንት (8) ሰዎች (ሶስት ከኦሮሚያ ክልል እና አምስት ከአዲስ አበባ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 217 ነው።

Related Post