አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በ2012/13 የምርት ዘመን 379 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ታቅዷል

በ2012/13 የምርት ዘመን 379 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ታቅዷል
በ2012/13 የምርት ዘመን 379 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ታቅዷል

በ2012/13 የምርት ዘመን 379 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንና ወደምርት ባልገቡ የተለያዩ ተቋማት የተያዙ መሬቶችን ወደምርት ማስገባት እና የመስኖ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2012/13 የምርት ዘመን 379 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንና ወደምርት ባልገቡ የተለያዩ ተቋማት የተያዙ መሬቶችን ወደምርት ማስገባት እና የመስኖ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ከተለያዩ ሚዲያዎች ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በኮሮና ቫይረስ መከላከል፣ በበልግ አፈፃፀም እና በመኸር ዝግጅት ላይ በዛሬዉ እለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በዓለማችን ብሎም በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ከወዲሁ የተጋላጭነቱን ስፋት በመለየትና እቅድ በማዘጋጀት የባለሙያውንና የአርሶ አደሩን ግንዛቤ በማሳደግ በምርት እድገት ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ከክልሎች ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

አቶ ኡመር በመግለጫቸው በቆላማ አካባቢዎች ስንዴን በመስኖ በማልማት የተገኘውን መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች ክልሎች በማስፋት ከ300 እስከ 350 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት በሀገር ደረጃ የሚፈለገውን የስንዴ አቅርቦት ለማሟላት ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በበልግ እርሻ 1.9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 60 በመቶ በዘር የተሸፈነ መሆኑንና ምቹ የአየር ሁኔታ ስላለ ቀሪው በግንቦት ወር የመጀመሪያዉ ሳምንት እንደሚጠናቀቅና ጥሩ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የመኸር ሰብል ምርት ዝግጅትን በተመለከተ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ሲሆን የግበዓት አቅርቦት እና ስርጭት እንዲሁም የመሬት ዝግጅት ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ኡመር በዘንድሮዉ የመኸር እርሻ ስራ የግብርና ስራችን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመከላከል እያንዳንዱ አርሶአደር ከቤተሰቡ ጋር በማሳዉ ላይ ተወስኖ የሚሰራና የኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚሰጠዉ በቤተሰብ ደረጃ እንደሚሆን እና የግንዛቤ መፍጠር ስራዎች የተለያዩ ሚዲዎችን መጠቀም ላይ እንደሚያተኩር አቶ ኡመር ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም በሀገራችን የተከሰተው የበረሀ አንበጣ በቀጣይ ወራት ሊያስከትል የሚችለውን የምርት ቅነሳ ለመከላከል የተሟላ የሰው ሀይል በማሰማራት በመኪና፣ በሄሌኮፍተር፣ በአውሮፕላን የታገዘ የመከላከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተውቀዋል።

በመጨረሻም፣ በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮች እና ባለሙያዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ግንዛቤ በመፍጠርና እየቀረበ ያለዉን ግብዓት በወቅቱ በማሰራጨት የተቀመጠዉን እቅድ ለማሳካት በትኩረት እንዲሰሩ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Related Post