አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተያዙ

በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተያዙ
በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ተያዙ

ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህጋዊ እቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ሀርዲስኮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ስራአስኪያጅ አቶ ፈረጃ አታላይ፣ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሞኒተር ውስጡን ባዶ በማድረግ እና በምትኩ አዳዲስ ላፕቶፖችን እና ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን በማስገባት እና መልሶ በማሸግ በህገወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ 100 ላፕቶፖች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተገኘው የፍተሻ ውጤት መሰረትም በሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን አቶ ፈረጃ ጠቁመዋል፡፡
ተፈፀመዉ የንግድ ማጭበርበር ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት ሲሆን በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑንም ምትክል ስራአስሊያጁ አስረድተዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ህገወጥ ድርጊቶች ህጋዊውን ነጋዴ ከትክክለኛው መስመር እንዲወጣ የሚያደርጉ እና መንግስት መሰብሰብ የሚገባውን ቀረጥ እና ታክስ እንዳይሰበስብ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

አቶ ፈረጃ አክለውም፤ የስሪት ሀገርን ማሳሳት፣ ህጋዊ እቃዎች ሽፋንን በማድረግ ህገወጥ እቃዎችን ማስገባት እና ሌሎች የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም ከህጋዊ መንገድ ያፈነገጠ ስራ የሚሰሩ አንዳንድ አስመጭና ላኪዎች እንዳሉ የጠቆሙት አቶ ፈረጃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር እና ፍተሻ ዓላማቸው እንዲከሽፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በቅርንጫፍ ጽ/ ቤቱ ባለፉት አምስት ወራት እቃዎች የጉምሩክ ስነ ስርዓት አጠናቀው ለነፃ ዝውውር ከተለቀቁ በኃላ የአስመጭዎችን የህግ ተገዥነት ለማረጋገጥ በድንገተኛ ፍተሻ እና የመረጃ ክፍሎች በተደረጉት የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች በየተለያዩ የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም መንግስት ሊያጣው የነበረ የቀረጥና ታክስ መጠኑ ከ320 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

Related Post