አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በእስራኤል በኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

በእስራኤል በኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ማሰባሰቢያ ተካሄደ
በእስራኤል በኢትዮጵያ ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ማሰባሰቢያ ተካሄደ

በእስራኤል የኢትዮጵያውያ ኤምባሲ የካቲት 12 ቀን 2014 ዓ.ም “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም” ማህበር ጋር በመተባበር ‘ገበታ ለወገን’ በሚል የተዘጋጀው የእራት ግብዣ በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በአሸባሪ ቡድኖች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ የሚውል ገንዘብ ማሰባሰብ ተችሏል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በእስራኤል የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ረታ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት “በእስራኤል የምትኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን /የቤተ እስራኤል ማህበረሰብ፣ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ወዳጆች በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በትህነግና በሸኔ ጥቃት ለደረሰባቸውና ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ በማሰባሰብና በመላክ ለአገራችን፣ ለወገኖቻችን ያላቸሁን አለኝታነት በመግለጽ እያደረጋችሁት ያለው ድጋፍና ትብብር በመንግስታችን ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጠው ነው።” በማለት ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።



ይህ መርሃ ግብር እንዲሳካ ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም” ማህበር አባላትና ተሳታፊዎችን አመስግነዋል። በማያያዝም በዓለምዐቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና ለማስቀረት በተካሄደው በቃ/#no more በሚለው ዘመቻ በእስራኤል ያሉት የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ፣ እንዲሁም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ወደ ሀገር ቤት በመሄድ ላደረጉት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህ ወቅት ”ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሞላ ሚካኤል ባደረጉት ንግግር እኛ በእስራኤል ያለን የዳያስፖራ አባላት አገራችን ፈተና በገጠማት ጊዜ በተቻለን አቅም ከጎኗ ልንቆም ይገባል። ይህንም ስናደርግ በትልቅ ፍቅርና ተስፋ በመሆኑ ሁሌም ሃገራችን በምታደርገው ጥሪ የበኩላችንን ለማበርከት ዝግጁ ነን በማለት፣ በቀጣይ ተመሳሳይ መርሐ ግብር ለማዘጋጀት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። አምባሳደር ረታ በራት ግብዣው ማጠቃለያ ለአስተባባሪዎች የምስጋና ምስክር ወረቀት በመስጠት ትብብሩ ለወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

(ምንጭ- የዉጪ ጉዳይ ሚኒስተር)

Related Post