አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚፈጽሙ ክፍያዎች በሳምንት 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደረሰ

በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚፈጽሙ ክፍያዎች በሳምንት 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደረሰ
በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚፈጽሙ ክፍያዎች በሳምንት 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደረሰ

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፌደራል መንግሰት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ጋር በኤሌክትሮኒክ ክፍያ አፈጻጸም ላይ በሚንስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደተገለጸው የፌደራል መንግሰት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሚፈጽሙት ክፍያ በሳምንት 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

በኢንተርኔት ባንኪንግ የተከናወኑ ክፍያዎች በጥቅምት 2014 ዓ.ም ሲጀመር በሳምንት 900 የነበሩት ክፍያዎች በአሁኑ ወቅት በሳምንት ከ12 ሺህ በላይ ክፍያዎች በኤሌክትሮኒክ ክፍያ ስልት እየተፈጸመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በውይይቱ መድረኩ እንደተገለፀው ከጥቂት መ/ቤቶች በስተቀር ሁሉም የፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ስርዓቱን በስራ ላይ እንዳዋሉና አንዳንድ መ/ቤቶች ክፍያዎችን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ማከናወን ደረጃ ላይ መድረሳቸው የተገለፀ ሲሆን፣ በርካታ መስሪያ ቤቶች 50 በመቶ ክፍያዎችን በኤሌክትሮኒክ ክፍያ በማከናወን ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የኤሌክትሮኒክ ክፍያውን መጠቀም ከጀመሩ በሁዋላ ጥቅሙን እና አስተማማኝነቱን በመረዳት ክፍያዎቻቸውን በቼክ፣ በጥሬ ገንዘብ፣ እና በደብዳቤ ከማከናወን ይልቅ ወደ ኤሌክትሮኒክ ክፍያዎች ዘዴ እያዘነብሉ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ስርዓቱ አለመግባት፣ የሂሣብ ሪፖርትና የመንግስት ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) የአፈጻጸም ሪፖርት በወቅቱ አለማቅረብ፣ ለመንግስት ገቢ መደረግ ያለበትን ገንዘብ በወቅቱ ያለማስገባት፣ አመታዊ የጥሬ ገንዘብ ዕቅድን በአግባቡ ያለማቀድና ከተደገፈው የጥሬ ገንዘብ ዕቅድ በላይ የመጠየቅ ችግሮች መኖራቸውንም ተስተውሏል፡፡

በአጠቃላይ የመንግስት የደመወዝ፣ የግዢና የአገልግሎት ክፍያዎችን በኤሌክትሮኒክ ክፍያ መፈጸም ቀልጣፋ፤ግልፅና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ከመስጠቱም ባሻገር የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያሻሻል መሆኑተመልክቷል፡፡

የፌዴራል መንግስት የኤሌክትሮኒክ ክፍያ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 71/2013 አምና የወጣ ሲሆን ከ2014 በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ጀምሮ የክፍያ ስርዓቱ ትግበራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

Related Post