አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 24 ሠዎች ኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 24 ሠዎች ኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 24 ሠዎች ኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 3,460 ላቦራቶሪ ምርመራ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው አሁን ላይ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 389 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በቫይረሱ ተያዙት 24 ሰዎች መካከል 12 የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 8 ደግሞ በሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆን አራቱ ግን የውጭ ጉዞ ታሪክም ሆነ ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አራት ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 122 ነው።

Related Post