አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,652 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 22 ሺህ 252 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 652 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 ሺህ 894 ደርሷል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 660 ሆኗል። ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኮቪድ-19 ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 509 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት 199 ሰዎች በፅኑ መታመማቸውንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 577 ሺህ 994 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

Related Post