አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በኔዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

በኔዘርላንድስ በሔግ ከተማና በአከባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውን ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ክብርት አምባሰደር ሒሩት ዘመነ ባደረጉት ንግግር ከኮቪድ-19 ስርጭት ጋር ተያይዞ በአዳራሽ የሚካሄዱ ስብሰባዎች ላይ የተጣለው ገደብ ተነስቶ በአካል በመገናኘት ስብሰባ ለማካሄድ በመብቃታችን እንኳን ደስ ያለን ካሉ በኋላ በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ ከኮሚኒቲዉ አባላት ጋር የሃሳብ ለውውት አድርገዋል።

በዚሁ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በተደረጉ አገራዊ ጥሪዎች፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት፣ ለታላቁ የኢትዮጵያ ጉዞ፣ ከኢድ እስከ ኢድ ፕሮግራሞች ለተደረገው ተሳትፎ እንዲሁም በአገራችን ያለው እውነታ እንዲታዎቅ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ለሚኖሩብት አገር መንግስት እና በአውሮፓ ደረጃ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላደረጉት የነቃ ተሳትፎ የዳያስፓራውን አባላት አመስግነው ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የዳያስፖራ አባላቱም በበኩላቸው ሚሲዮኑ መድረኩን በማዘጋጀቱ አመስግነው፣ ለአገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማስቀጠል በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ የመረጃ ስርጭት በተጠናከረ መልኩ እንዲዳረስ፣ ማህበረሰቡን የሚከፋፍሉ አካሄዶችን ተከታተሎ ወቅታዊ እርምጃ እንዲወሰድ በማሳሰብ ማብራሪያ የሚሹ ጉዳዮችን አንስተዋል።

በተነሱት ጉዳዮች ላይ በክብርት አምባሳደር ሒሩት ዘመነ እንዲሁም በሚሲዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ በርይሁን ደጉ ዝርዝር ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥተዋል፡፡

በዚህ አጋጣሚም አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በጽናትና መጻእይ ብሩህ ተስፋን በመሰነቅ በችግር ውስጥ የሚገገኙ ወገኖቻችንን ለመርዳትና በአገር ጉዳይ ላይ ተቀራርቦ በመሥራት በውጭ ሃይሎች የተጋረጡብንን አደጋዎች ለመመከት የተጠናከረ የአድቮኬሲና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሥራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Related Post