አርእስተ ዜና
Sun. Jan 26th, 2025

በቱኒዚያ አይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ወጡ

በቱኒዚያ አይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ወጡ
በቱኒዚያ አይሲቲ ውድድር ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶስተኛ ወጡ

የሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ክፍለ አህጉራዊ የፍጻሜ ውድድር ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በቱኒዚያ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት መካከል በኮምፒውቲንግ ትራክ (Computing Truck) የተወዳደሩት የሶስት ተማሪዎች ቡድን ሞሮኮ እና ቱኒዚያን ተከትለው ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል።

በጠቅላላ ውድድሩ ከኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ አልጄሪያ፣ ቱኒዝያ፣ ሊቢያ፣ ግብፅ እና ሞሮኮ የተውጣጡ 90 ተማሪዎች በተለያየ የውድድር ዘርፍ ተሳታፊ ሆነዋል። በውድድሩ ሶስተኛ ደረጃን የያዙት ተማሪዎች የሁዋዌን ዘመናዊ ስልክ የተሸለሙ ሲሆን የተቀሩት 6 ተማሪዎች በተሳትፏቸው የሁዋዌ ታብሌቶችን ተሸልመዋል። ኩባንያው ለተማሪዎቻቸው ድጋፍ ላደረጉ መምህራንም እውቅና ሰጥቷል። እነዚህ ሦስት ተማሪዎች ሁለቱ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አንድ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው።

የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ እንዳሉት ሁዋዌ ተማሪዎች በጤናማነት የሚወዳደሩበት፣ ሀሳብ የሚለዋወጡበት፣ የአይሲቲ እውቀታቸውን እና የተግባር ክህሎታቸውን የሚያጎለብቱበትን መድረክ ማመቻቸቱ ተማሪዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና መድረኮችን በመጠቀም አዳዲስ ፈጠራዎችን የመፍጠር አቅማቸውን እንደሚያሳድጉበት ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።

ውድድሩ በሰሜን አፍሪካ ክልል (ሰሜን፣ ምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ) ከዘጠኙ ሀገራት የተውጣጡ 30 ቡድኖችን ይዟል። ኢትዮጵያ በ3 ቡድኖች በተከፋፈሉ በ9 ተማሪዎች ተወክላ የነበረ ሲሆን በ3 የተለያዩ ምድቦች፡ ክላውድ ትራክ፣ ኮምፒውቲንግ ትራክ እና የኔትወርክ ትራክ ውድድሮች ላይ ተሳትፈዋል።

በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑት ተማሪዎች በ2024 በቻይና በሚካሄደው እና ከ500 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ20,000 በላይ ተማሪዎችን በሚሳተፉበት የመጨረሻው ምዕራፍ ውድድር ላይ የመሳተፍ እድል ይኖራቸዋል። ሁዋዌ አይሲቲ ውድድር ለአለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተነደፈ የአይሲቲ ክህሎት ማሳደጊያና ማበልጸጊያ መድረክ ነው።

Related Post