አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

በሺዎች ተጀምሮ በሚሊዮን ብር ያደገዉ የታክስ ክፍያ

በሺዎች ተጀምሮ በሚሊዮን ብር ያደገዉ የታክስ ክፍያ
በሺዎች ተጀምሮ በሚሊዮን ብር ያደገዉ የታክስ ክፍያ

አምዮ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና እርሻ መሳሪያዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር ለመንግስት የሚያስገባዉ ግብር በአመት ከመቶ ሺዎች ወደ ሚሊዮን ብሮች መሸጋገሩን ገልጿል፡፡

የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢብራሂም ያሲን በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ እንደተናገሩት ከዉጪ ለሚያስመጡዋቸዉ እቃዎች ቀረጥ፡ለሰራተኛ ጡረታ የሚከፈል እንዲሁም አመታዊ የስራ ግብርን ጨምሮ ከሺ ብሮች ወደ ሚሊየን ብሮች ለመንግስት አመታዊ ግብር እንደሚከፍል ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በሃገራችን የሚገኙ ኢንደስትሪዎች ጥገና በሚፈልጉበት ሰአትም ደርጁቱ ስለሚያግዝና በፊት ከነበረዉ የስራ መጉላላትን ከማስቀረት አንፃር ለስራ ምርታማነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

ባለፉት አመታት የኢትዮጵያ የታክስ ገቢ እየጨመረ እንደመጣ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ለማሳያነትም ከሐምሌ1/2011 እስከ ሚያዚያ 30/2012 አ.ም ባለዉ አስር ወራት ዉስጥ ሀገሪቱ የሰበሰበችዉ የታክስ ገቢ198.5 ቢሊዮን ብር እንደሆነ የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ይህም አሃዝ ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘዉ አጠቃላይ የታክስ ገቢ በ35.3 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=fferdlFz9Ss[/embedyt]

Related Post