አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

በሳውዲ የሚኖሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ ነው

በሳውዲ አረብያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ በበርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ወደአገራቸው እየተመለሱ ነው።

በዛሬው ዕለትም 400 ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል። በቀጣይ ሰዓትም ሌሎች በረራዎች ይኖራሉ ተብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጐጌ ተስፋዬና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ በትኩረት እየስራ መሆኑ ይታወቃል።

Related Post