አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ መሆኑ ተገለጸ

በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ መሆኑ ተገለጸ
በርካታ የቻይና ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ክበርካታ የቻይና ኩባንያዎች ጋር በተለያዩ የልማት ዘርፎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ተገለጸ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን መሆኑን የገንዘብ ሚኒስተር ገለጸ። “የቻይና መንግስት ባድረገለት ጥሪ መሰረት በቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ላይ በመሳተፍ ላይ ያለው በአቶ አህመድ ሽዴ የሚመራውና ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የገንዘብ ሚንስትር ዲኤታን የያዘው የገንዘብ ሚንሰቴር ልዑካን ቡድን በቆይታው ከፎረሙ በተጓዳኝ ከቻይና አበዳሪ ተቋማት በኢትዮጵያ ማዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ ከፍተኛ የልማት ስራዎች በመስራት ላይ ካሉ እንዲሁም ወደፊት መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ በኢትዮጵያ መሳተፍ ከሚፈልጉ ካምፓኒዎች ጋር እጅግ ፍሬያማ ውይይት አድርጓል፡፡” ሲል መግለጫ ያወጣው የገንዘብ ሚኒስተር ነው።

“በኢትዮጵያ ልማት ለሚሳተፋ የቻይና ድርጅቶች የሚደረገው የመንግስት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ በውይይቱ ለተሳተፋ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያና የቻይና የኢንቨስትመንት ፎረም በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የስብሰባ አዳራሽ ተካሂዳል፡፡ፎረሙ በገንዘብ ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ የመግቢያ ንግግር ተከፍቷል፡፡ክቡር ሚንስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያና ቻይና ያለቸውን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂክያዊ አጋርነት በአሁኑ ወቅት ወደ ሁሉን አቀፍ የልማት ትብብር መሸጋገሩን ገልፀዋል፡፡”

“በፎረሙ ላይ የተሳተፋት የማዕድን ሚንስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያለውን ሰፊ ሀብትና የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፓሊሲን በተመለከተ ለፎረሙ ተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡ በርካታ የቻይና ካምፓኒዎች በተለያዩ የልማት ዘርፎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራርመዋል፡፡”

ከነዚህም መካከልም ከቻይናው ኤክሲም ባንክ ሊቀመንበር ከሚስተር ውፍሊን እና ከባንኩ ሀላፊ ዋኑ ጋር በተደረገ የጋራ ስብሰባ ላለፋት ዓመታት በባንኩ የተያዘው የብድር ክፍያ ለፕሮጀክቶች በሚለቀቅበትና የብድር ክፍያ ሽግሸግ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከባንኩ የስራ ኃላፊዎች አበረታች ምላሽ ተገኝቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከቻይና ልማት ባንክ ሚስተር ዋንግ ዎልዶንግ፣ ከምክትሎቻቸው እና ከተለያዩ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ስብሰባ ቀደም ሲል የተጀመረው የብድር ክፍያ ማራዘሚያ ድርድር በቶሎ በሚቋጭበትና ባንኩ በቀጣዩ የአገራችን የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች በሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ከዚህም ሌላ ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ መዋዕለነዋያቸውን ከፈሰሱና ወደፊት በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ስራዎች መሳተፍ ከሚፈልጉ ካምፓኒዎች የስራ ኃላፊዎች ጋር የተናጥል ውይይት አድርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም ከቻይና መንገድና ድልድይ ኮንስትራክሽን ድርጅት (CRBC)፣ CGCOC እና CGGC ጋር ፍሬያማ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ካምፓኒዎቹ በቀጣይ በኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ መሆናቸውን በመግለፅ ከመንግስት እንደሁልግዜውም የሚደረግላቸው ድጋፍ እናዳይለያቸው ጠይቀዋል፡፡

Related Post