አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

በመንግስት ከህወሀት ጋር ድርድር አልጀመረም

በመንግስት ከህወሀት ጋር ድርድር አልጀመረም
በመንግስት ከህወሀት ጋር ድርድር አልጀመረም

በመንግስት ከህወሀት ጋር ድርድር አለመጀመሩን ጠቅላይ ሚነስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡

በመንግስት በኩል ከህወሀት ጋር እስካሁን የተጀመረ ምንም አይነት ድርድር አለመኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል፡፡



ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግስት በኩል ከህወሀት ጋር የተደረገ ድርድር እንደሌለ ነገር ግን ድርድር አልተደረገም ማለት ድርድር አያስፈልግም ማለት እንዳልሆነ አስገንዝበዋል፡፡

አክለውም የምናካሂደው ጦርነትም ሆነ ድርድር ዓላማ ኢትዮጵያን ማፅናት እንደሆነ ጠቁመው ሀገርን በሚያፈርስ በማንኛውም መንገድ ድርድር እንደማይደረግም ነው የተናገሩት፡፡

ይሁን እንጂ ህወሀት በጦርነት ማሸነፍ እንደማይቻል ካመነና ቀልብ ከገዛ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ህልውና በማይፈታተን ሁኔታ ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡



ታስረው የተፈቱትን ከፍተኛ የህወሀት አመራሮች በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከዚህ ቀደም በም/ቤቱ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎች ‹‹የታሰሩት ለምን አይፈቱም? እንጂ ለምን ተፈቱ?›› የሚል እንዳልነበርና ይህም በራሱ ለውጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የህወዓት አመራሮችን መፍታት ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ለዘላቂ ሰላም እና የተገኘውን ድል ለማፅናት ሲባል መሆኑንም ነው ያብራሩት፡፡

Related Post