አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በህገ-ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ ማዕድን በቁጥጥር ስር ዋለ

በህገ-ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ ማዕድን በቁጥጥር ስር ዋለ
በህገ-ወጥነት ሲዘዋወር የነበረ ማዕድን በቁጥጥር ስር ዋለ

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አራት ኪሎ ግራም የሚመዝን ማግናታይት የተባለ ማዕድን በሀረር ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደረሰው መረጃ እና በተደረገ የክትትል በሀረር ከተማ ማእድኑን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሶስት ተጠርጣዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል በዚህ ስራ ላይ ተሳትፎ ላደረጉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የኢንለጀንስ ባለሙዎች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉምሩክ ኮሚሽን ልባዊ ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Related Post