አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

መከላከያ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ተቆጣጠረ

መከላከያ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ተቆጣጠረ
መከላከያ አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ተቆጣጠረ

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አክሱምን፣ አድዋንና አዲግራትን ተቆጣጠረ ።

መከላከያ እንቲጮንና አዲግራትን ተቆጣጥሮ ይገኛል። ዛሬ ኅዳር 12 2013 አዲግራት ከሕወሓት ጁንታ ነጻ ወጣች። የመከላከያ ሠራዊታችን ዛሬ በጠዋቱ የሕወሓትን ጁንታ ኃይል ድል አድርጎ የአዲግራት ከተማን ሙሉ በሙሉ ነጻ አውጥቷታል። የመከላከያ ሠራዊታችን በአሁኑ ጊዜ ወደ መቀሌ እያመራ ነው።አያሌ የጁንታው ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከድተው ከጁንታው ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም ይገኙበታል።

በምዕራብ ግንባር የሕወሐት ጁንታን ኃይል እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሐት ኃይል ገጥሞት ነበር። ሰለህለሃ ላይ የመሸገው የጁንታው ኃይል መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከል አድርጓል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የጁንታውን ተከላካይ ኃይል ሠብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ድል ሆኗል።

(ምንጭ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ)

Related Post