አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

መርዛማው ዛፍ ለኢንዱስትሪዎች የሀይል ምንጭነት ሊውል ነው

መርዛማው ዛፍ ለኢንዱስትሪዎች የሀይል ምንጭነት ሊውል ነው
መርዛማው ዛፍ ለኢንዱስትሪዎች የሀይል ምንጭነት ሊውል ነው

የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል በ3 ዓመታት ተግባራዊ የሚሆን ድጋፍ ፕሮሶፒስ ጁሊፎራ የተባለውን የዛፍ ዝርያ ለሲሚንቶና ትላልቅ ፋብሪካዎች የሀይል ምንጭነት መጠቀም የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪዎች ለማቃጠያነት ይጠቀሙበት የነበረውን የድንጋይ ከሰል 40 በመቶ በባዮማስ በመተካት ከውጭ ይገባ የነበረ ከፍተኛ የሆነ የድንጋይ ከሰል ፍጆታን እንደሚቀንስ በጥናት ተረጋግጧል፡፡

ፕሮጀክቱ ከአየር ንብረት ለውጥ አንጻር ከፍተኛ የሆነ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀትን በመቀነስና ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የተገለጸ ሲሆን ወራሪ ዛፉ በሚገኝበት አካባቢ ላለው ማህበረሰብ ደግሞ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያደርሰውን ተጽኖ መቀነስ የሚችል ነው፡፡

ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ በአካባቢው አጠራር ደርጊ ሀራ የተባለው የዛፍ ዝርያ ድርቅን የሚቋቋም የበረሀ ዛፍ ተብሎ በደርግ ዘመን ወደ አካባቢው እንደገባ በመናገር አሁን ላይ እያደረሰባቸው ካለው ጉዳት አኳያ ዛፉን የሚያጠፋ ፕሮጀክት ከመጣ በአላቸው አቅም ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአፋርና ሱማሌ ክልሎች ከ1.2 እስከ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ሸፍኖ እንደሚገኝ በጥናት ተረጋጧል፡፡

ፕሮጀክቱን የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል በዋናነት እያሰተባበረ የሚገኝ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አምራቾች ዘርፍ ማህበር፤ የአፋርና ሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት፣የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር፤ የኢፌዴሪ መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የዚህ ፕሮጀክት ዋና ባለድርሻ አካላት ናቸው፡፡

በሰኔ ወር መጀመሪያ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ ክቡራን ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በአፋር ክልል አሚቫራ ወረዳ መልከሰዴ ቀበሌ 2000 ሄክታር መሬት ላይ የሙከራ ትግበራ ማሳጀመሪያ ፕሮግራም ይከናወናል፡፡

Related Post