አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የይዞታ መለየት ስራ ጀመረ

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የይዞታ መለየት ስራ ጀመረ
መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የይዞታ መለየት ስራ ጀመረ

መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ የሚገኙ 20 የመሬት ይዞታዎች የሚካሄደው የሙከራ የይዞታ መለየት እና መቀየስ ስራ አፈፃፀም 95 በመቶ እንደተከናወነ ባደረገው ግምገማ አረጋገጠ።

በሃገራችን የተጀመረዉን ለዉጥ ዘላቂ ለማድረግ በአዲስ መልክ ከተቋቋሙ የፌዴራል ስራ አስፈጻሚ ተቋማት መካከል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን (መባልኮ)
አንዱ ነዉ። መንግስት ሃገሪቱ ያላትን የመሬት ሃብት መረጃ በአግባቡ በማደራጀት ይዞታዎችን በማልማትና በማስተዳደር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ለማስቻል የተለያዩ እርምጃዎችን በመዉሰድ ይገኛል። በዚህም መሰረት ኮርፓሬሽኑ በመላው ሃገሪቱ ያለውን የፌዴራል መሬት ይዞታን ለማልማትና ለማስተዳደር ያመች ዘንድ የመሬት መረጃዎችን ለማሰባሰብና የይዞታ ካርታ ስራ ለማከናወን ከጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ጋር ‘የፌዴራል መሬት ይዞታዎች ካርታ ዝግጅት’ በሚል የጋራ መግባቢያ የሰነድ ስምምነት በ መጋቢት ሁለት 2012 በመፈራረም ስራው በፕሮጀክት ደረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

በዛሬዉ እለት ግንቦት 12 2012 ዓ.ም የፕሮጀክቱን የመጀመሪያ ደረጃ የገመገሙት የተቋማቱ ሃላፊዎች በአዲስ አበባ ንዑስ ፕሮጀክት በሁሉም ክ/ከተሞች ከሚገኙ ወደ ሁለት መቶ ከሚጠጉ የመሬት ይዞታዎች ውስጥ በ 20 የመሬት ይዞታዎች የሚካሄደው የሙከራ የይዞታ መለየት እና መቀየስ ስራ በተያዘዉ እቅድ 19 ለሚሆኑት የድንበር መለየትና የኮኦርድኔት ነጥቦችን መልቀም ፣ በይዞታው ስር ያሉትን የህንጻ አገልግሎት መለየትና መመዝገብ እና የቁራሽ መሬቶችን ጂኦግራፊያዊ (spatial feature) መረሰስ ስራዎች ክንዉን ገምግመዋል፡፡

በዕቅዱ መሰረት የመስክ ሥራው አፈፃፀም 95 በመቶ ሲሆን በተቋማት አለመተባበር፡ የመረጃ እጥረት እንዲሁም በወቅታዊ የCOVID-19 ወረርሺኝ ምክንያት አጠቃላይ አፈፃፀሙ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ማድረጉን በዛሬዉ እለት ገምግመዋል፡፡ እሰካሁን የተሰሩት የፓይለቲንግ ስራዎች በኣንድ ቡድን የተሰሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ከ 5 ያላነሱ ተጨማሪ ቡድኖችን በማዋቀር እንዲሁም ለተቋሞች ከፍተኛ ግንዛቤን በማስጨበጥ ስራውን በታቀደለት ጊዜ እንዲያልቅ በአፋጣኝ ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለመግባት የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተለዩት ይዞታዎች መካከል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪይሽን ባለስልጣን ፡ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴ

Related Post