አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ለ2015/16 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች

ለ201516 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች
ለ201516 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ደረሰች

ግሬት ኮምፎርት /MV GREAT COMFORT/ የተባለቸው ግዙፍ መርከብ ለ2015/16 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባው የአፈር ማዳበሪያ የመጀመሪያውን ከ57ሺ 295 ሜትሪክ ቶን ኤን. ፒ.ኤስ /NPS/ የአፈር ማዳበሪያ አይነት ከሞሮኮ ጭና የመጣች ሲሆን፣ ትናንት ታህሳስ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጅቡቲ ወደብ ገብታ የማራገፍ ስራዋን እያከናወነች ነው፡፡

በሶስተኛው የኦፕሬሽን ሽፍት /በምሽት ሽፍት/ ከ2ሺ 3መቶ ሰባ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያን ወደ ሀገር ውስጥ መላክ ተችሏል፡፡
ኢባትሎአድ የማጓጓዝ ስራውን በበቂ ዝግጅት በመጀመሩ መርከብ ወደብ በገባች በሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ የመጫንና የመጓጓዝ ስራ በፍጥነት ማከናወን አስችሎታል፡፡

በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ እያንዳንዳቸው 60 ሺ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት ግዙፍ መርከቦች ጅቡቲ እንደሚደርሱ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው የአፈር ማዳበሪያን በታቀደለት ጊዚ አጓጉዞ በስኬት ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡

Related Post