አርእስተ ዜና
Tue. Dec 24th, 2024

ግዙፏ ዓባይ ፪ መርከብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጅቡቲ ደረሰች

ግዙፏ ዓባይ ፪ መርከብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጅቡቲ ደረሰች
ግዙፏ ዓባይ ፪ መርከብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጅቡቲ ደረሰች

በግዙፍነቷም ሆነ በዓይነቷ የመጀመሪያ የሆነችው ዓባይ ፪ መርከብ በኢትዮጵያ ባንዲራ ተመዝግባ ወደ አገልግሎት ከገባችበት ሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ይዛ ትናንት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ጅቡቲ ወደብ ደርሳለች፡፡

ዓባይ ፪ 60ሺህ ሜትሪክ ቶን ኤን. ፒኤስ እና ኤን.ፒኤስ.ቢ የአፈር ማዳበሪያ ዓይነቶችን ነው ከሞሮኮ ጆርፍ ላስፈር ወደብ ወደ ጅቡቲ ያመጣችው፡፡
መርከቧ በአሁኑ ሰዓት በጊዜያዊ የኪራይ ኮንትራት /Time Charter/ አገልግሎት ተሰማርታ በአውሮፓ፣ በኤዥያ እና በአፍሪካ አህጉራት ባሉ ወደቦች መካከል የሌሎች ሀገራት ጭነቶችን በማጓጓዝ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እያስገኘች መሆኑን ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የምርት ዘመኑን የአፈር ማዳበሪያ በባሕር አጓጉዞ እስከ ጅቡቲ የሚያደርሰው ስካይ ፍዩዥን (Sky Fusion) የተባለ ዓለም-አቀፍ የመርከብ ድርጅት ሲሆን፤ ዓባይ ፪ መርከብም የኢትዮጵያን ጭነት ጅቡቲ ያደረሰችው ለዚሁ ድርጅት በጊዜያዊነት በኪራይ እየሰራች መሆኑ ታውቋል።

በቀጣይ መርከቧ የኮንትራት ጊዜዋን ስታጠናቅቅም የሀገራችንን ጭነት ወደ ማጓዝዝ ስራ ትሰማራለች ተብሏል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት 73 ሺህ 800፣ 83, 400 እና 51,000 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ግዙፍ መርከቦች ጅቡቲ እንደሚደርሱም ተገልጿል፡፡
ምንጭ – ኢዜአ

Related Post