አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የጦር መሳሪያዎችና 18 ሚሊዮን ብር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

የጦር መሳሪያና 18 ሚሊዮን ብር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
የጦር መሳሪያና 18 ሚሊዮን ብር የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

የጦር መሳሪያ ጨምሮ ሌሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ።

ከአዲስ አበባ ወደ ቆቦ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 03- A23652 መለስተኛ የጭነት ተሸከርካሪ 3 (ሶስት) ህገ ወጥ ሽጉጦች ሴራሚክ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ መስከረም 11 ቀን 2013 ተይዟል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪው እና ረዳቱ በቁጥጥር ስር ውለው በክልሉ ፖሊስ ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል 18 ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር (18,111,599) ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ኮንትሮባንድ የሆኑ ደረቅ ጫት፣ እህል፣ ትምባሆ እና ሌሎች ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ እና መቅረጫ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 13 ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ደረቅ ጫት ሰሌዳ ቁጥር ኮድ3-61696 እና ኮድ3-49716 ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ኮንትሮባንድ የሆነ ደረቅ ጫት ተይዞ ያቤሎ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ገቢ ተደርጓል፡፡ 8,980 ኪ.ግ መጠን እንዳለው የተገለጸው ደረቅ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሲጓጓዝ እንደተያዘ ከሞያሌ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም በተለምዶ “ሻንፖ” ተብሎ በሚጠራ የጭነት መኪና ተጭነው ከሱማሌላንድ ወደ ጅጅጋ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በሌሊት ሊገባ ሲል በቱሉጉሌድ አካባቢ እንዲሁም ከቀብሪበያህ በኩል በኤፌሳር እና ሚኒባስ ተጭኖ ሊገባ የነበረ የውጭ ሀገር ማሽላ እና ዘይት 3,500,000 ብር አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በጉምሩክ ሰራተኞች እና በፌዴራል ፖሊስ አባላት አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

እንዲሁም በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች በእርዳታ የገባ ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋው 1,141,599 ብር የሆነ ማሽላ፣ ስንዴ እና አተር ክክ ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በመጓጓዝ ላይ እያለ በጅማ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስር በሚገኘው በሆሌና በባሮ ቀላ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሊያዝ ችሏል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የምትገኙ የጉምሩክ ሰራተኞች ለሀገራችን እና ለህዝባችን ደህንነት ለፀሐይና ብርድ ሳትበገሩ ኃላፊነታችሁን የድርሻችሁን እየተወጣችሁ ስለሆነ የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ኮንትሮባንድን የመከላከል ስራው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣው በህዝባችንም ተሳትፎ ጭምር ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም ድጋፋችሁ እና ተሳትፎአችሁ እንደማይለየን እንተማመናለን፡፡
(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post