አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ስራ ሊጀምር ነው

የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ስራ ሊጀምር ነው
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ስራ ሊጀምር ነው

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ውስጥ የሚገኙና በተለያዩ የማምረቻው ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሀገር በቀልና አለም አቀፍ ባለሀብቶች ያሉበትን የምርት እንቅስቃሴን የጎበኙ ሲሆን አሁን ላይ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና በሙሉ አቅሙ ስራ ለመጀመርና የሎጀስቲክስና የንግድ ኢንቨስትመንቶችን ማስተናገድ በሚችልበት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን በአጭር ግዜ ዉጤታማ ለማድረግና በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ እንዲገባ ያከናወናቸው ስራዎች አበረታች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ነፃ ንግድ ቀጣናው በስራ እድል ፈጠራ፤ ተኪ ምርቶችን በማምረት፤ በቴክኖሎጂና በእውቀት ሽግግር የደረሰባቸው አበረታች ውጤቶች የሚደነቁ ናቸዉ ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በቅርቡ በሙሉ አቅሙ ስራ እንዲጀምር በሎጀስቲክስ በንግድ በገቢና ወጪ ዙሪያ የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ ገልጸው ሰሞኑን እየተካሄደ የሚገኘው የባለድርሻ አካላት ውይይት ግብዓት እንደሚሆንም ጠቁመዋል። በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የኮርፖሬሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።

Related Post