አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የዘጠኝ መቶ ሺህ ዶላር የህክምና ቁሳቁስ ለሶማሊ ክልል ተበረከተ

የዘጠኝ መቶ ሺህ ዶላር የህክምና ቁሳቁስ ለሶማሊ ክልል ተበረከተ
የዘጠኝ መቶ ሺህ ዶላር የህክምና ቁሳቁስ ለሶማሊ ክልል ተበረከተ

አርት ፋውንዴሽን ከግሎባል ሜዲካል ኤይድ ጋር በመተባበር የተለያዩ ለጤናው ዘርፍ የሚውሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ለሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ አስረክበዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሴ አህመድ በድጋፉ የተለያዩ የጤና መሳሪያዎችን እንደተረከቡ ገልጸው፤ ከነዚህም መካከል ለኩላሊት እጥበት የሚያገለግል የዲያለሲስ ማሽን፣ አልጋዎች፣ ዊልቸርና የተለያዩ የሜዲካል እቃዎች እንደሚገኙበትም ገልፀዋል።



ድጋፉ በማህበር ከተደራጁ የግብረሰናይ ድርጅቶች ሲገኝ ይሄ የመጀመሪያው መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ሙሴ እንደነዚህ አይነት ድጋፎች በውጪ በሚገኙ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በይበልጥ በአሁኑ ሰአት በክልሉ የተፈጠረውን ድርቅ በመገንዘብ ከህዝባቸው ጎን በመቆም ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የአርት ፋውንዴሽን ሀላፊ ወ/ሮ ነስቲሃ አሊ በበኩላቸዉ እንደነዚህ አይነት ድጋፎችን ከዚህ በፊትም በሶማሊያ፣ በኬኒያ፣ ሶማሊላንድና ጁባላንድ ማድረጋቸውን ገልፀው በዚህ በሶማሊ ክልል ሲያደርጉ የመጀመሪያ እንደሆነና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለድርሻ አካላት እና የዲያስፖራው መቀናጀት አስፈላጊ እንደሆነም ገልፀዋል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ አስታውቋል።



የክልሉ ጤና ቢሮ ድጋፉን ላበረከቱት አርት ፋውንዴሽንና ግሎባል ሜዲካል ኤድ የእውቅና ሰርተፍኬት ያበረከተ ሲሆን፤ በፕሮግራሙ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳዬች ቢሮ ኃላፊ ፣ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና ሌሎች የስራ ሀላፊዎችም ተገኝተዋል።

ምንጭ – ኢ.ፕ.ድ

Related Post