አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

ለኢትዮጵያ ሀይል አቅርቦት፣ ጤና፣ የቤት ልማት እና በፋይናንስ ዘርፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አሕመድ ሽዴ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተርን ክብርት ጁሞኬ ጃጉን ዶኩሙን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የዓለም ገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ለማሳደግ እያደረገ ስላለው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸው ተቋሙ የግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር መሰረት ለጣሉ ፕሮጀክቶች የቴክኒክ እና የኢኮኖሚ አዋጪነት ያላቸው ጥናቶች እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘፍን ለግሉ ዘርፍ የመክፈት ሂደት ላይ ለማስፈፀም በሚያደረገው ጥረት ላይ ተቋሙ ያሳየውን ድጋፍ በሌሎች ዘርፎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክብርት ጁሞኬ ጃጉን ዶኩሙ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው አስታውሰው፥ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ የግሉን ዘርፍ ኢንቨስትመንት እየደገፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በቀጣይም በሀይል አቅርቦት፣ በጤና፣ በቤት ልማት እና በፋይናንስ ዘርፎች ቅድሚያ በመስጠት ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም የኢትዮጵያ መንግሥት የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የባንኩን ዘርፍ ለውጭ የፋይናንስ ተቋማት የመክፈት ሂደት ላይ ተቋሙ ድጋፍ እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

(ምንጭ- ኢቲቪ)

Related Post