አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ70 መስጂዶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ70 መስጂዶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ70 መስጂዶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ

በአዲስ አበባ ከተማ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መስጂድ ግንባታ ለማካሄድ መሠረት ድንጋይ ተቀመጠ ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አዲስ ለሚገነባው አለም አቀፍ መስጂድ 30ሺህ ካሬሜትር ቦታን በማስረከብ የመስጂዱን ግንባታ አስጀምረዋል ።

በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠለትን መስጂድ ጨምሮ በከተማዋ ለሚገኙ 70 መስጂዶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሀጂ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ እና ለአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሱልጣን አማን አስረክበዋል ።

ይህ የዓለምአቀፍ መስጊድ የግንባታ ቦታ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የተሰጠ የኢድ በዓል ስጦታ ነው ያሉት ኢንጅነር ታከለ ከቀናት በኋላ የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለለፍ በዓሉን በመረዳዳት እና እርስበእርስ በመደጋገፍ ማክበር እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሀጂ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ ከጠቅላይ ከሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጀምሮ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የለውጡ አመራሮች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Related Post