አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

የአንበጣ መንጋ ወረራን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላኖች ሥራ ላይ መሆናቸው ተገለፀ

የአንበጣ መንጋ ወረራን ለመከላከል ስድስት አውሮፕላኖች ሥራ ላይ መሆናቸው ተገለፀ

በመጪዎቹ ወራት የአንበጣ መንጋ በሀገሪቱ ሊፋፋ እንደሚችል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የመንጋውን መስፋፋት ለመግታት ስድስት አውሮፕላኖችን ማሰማራቱን ገለፀ።

በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጤና አጠባበቅ ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ወልደሃዋርያት አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የክረምት መግባት ለአንበጣ መራባት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር የመከላከል ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአውሮፕላን፣ በተሽከርካሪ በሚጠመዱ መሳሪያዎች እና በሰው ሃይል በመጠቀም የኬሚካል ርጭቶችን በማድረግ ላይ መሆኑን አመልክ ተው፣ የመከላከል ሥራው በመንግስት እና በአጋዥ ድርጅቶች ቅንጅት አንበጣ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በስፋት እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ወልደሐዋርያት ገለፃ፤ የአንበጣ መንጋ ወረራው ከ2011 ዓ.ም ሰኔ አጋማሽ ጀምሮ በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ በሰሜን ምሥራቅ፤ አፋር፣ አማራና ትግራይ አካባቢዎች፣ በምሥራቅ ኦሮሚያ የተከሰተ ሲሆን ከህዳር 2012 ዓ.ም ወር ጀምሮ በደቡብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያና ደቡብ ክልል አካባቢዎች ተሰራጭቷል። በአሁኑ ጊዜ በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋው እየታየ ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ አካባቢ ከኬንያ የሚመጣ የአንበጣ መንጋ ታይቷል።

አሁን የሚታዩት የትንበያ ውጤቶች ወረራው እንደሚስፋፋ ነው። ከዚህ በፊት አንበጣ በተከሰ ተባቸው አካባቢዎች አዲስ የአንበጣ መንጋ እየተፈ ለፈለ ነው። ይሄ የአንበጣ መንጋ ከዚህ በፊት ወዳልነበረባቸው አካባቢዎችም ይዛመታል። የርጥበት ወራቶች ለተፈለፈሉት አንበጣዎች የሚመገቡት ስለሚያስገኝ መራባቱ አስከፊ ወረራ ላይ እንዳይደርስ የመከላከል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

(ምንጭ-አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2012)

Related Post