አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የህወሃት ጁንታ ጥቃት የቡድኑን የእናት ጡት ነካሽነትያሳያል ተባለ

የህወሃት ጁንታ ጥቃት የቡድኑን የእናት ጡት ነካሽነትያሳያል ተባለ
የህወሃት ጁንታ ጥቃት የቡድኑን የእናት ጡት ነካሽነትያሳያል ተባለ

የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር አዛዥ ብ/ጄ ናስር አባዲጋ ፣ እብሪተኛው የህወሃት ጁንታ የከፈተብን ጥቃት የቡድኑን የእናት ጡት ነካሽነት በትክክል የሚያሳይ እንደ ነበር ተናገሩ፡፡

ለሰላሳ ሰዓታት ፣ ከጁንታው ፣ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ እንዲሁም ከውስጥ ተልዕኮ ተቀባይ ባንዳዎች ጋር ውጊያ እንዳደረጉ የሚናገሩት ብ/ጄ ናስር ፣ በቀደሙት ሃያ ሁለት አመታት በትግራይ ክልል ቆይታችን ለህብረተሰቡም ሆነ ለአካባቢው እድገት ላበረከትነው አስተዋፅኦ ሽልማታችን ከከሀዲው ቡድን ይህ መሆን አልነበረበትም ብለዋል ፡፡

ቀደም ብሎ በ4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ላይ ተኩስ እንደተከፈተባቸው መረጃ ደርሷቸው ስለነበረ በውስን ጊዜ ውስጥም ቢሆን የጥንቃቄ እርምጃዎችን ወስደናል ብለዋል፡፡ በጥቅምት 23 ዳጉሳ ሲያጭድ በዋለው ሰራዊታችን ላይ በ24 ተኩስ ተከፍቶበታል ፡፡ ውጊያው ከውስጥም ፣ ከውጭም በሁለት አቅጣጫ ነበር ያሉት ጄነራል መኮንኑ ፣ በተለይ ከውስጥ ተልዕኮ ተቀብለው ከከሃዲው ቡድኑ ጋር ሲሰሩ የነበሩ የትግሪኛ ተናጋሪዎች ፣ በሰራዊታችን ላይ የፈጠሩት ጫና እጅግ ከባዱ ነበር ብለዋል ፡፡

እንደ ብ/ጄ ናስር ፣ ሰራዊታችን ከነበረው ጫና ተላቆ ዳግም ለመደራጀት በባድመ በኩል ወደ ኤርትራ ማፈግፈግ ግድ ነበር ፡፡ ወደ ኤርትራ ካፈገፈጉ በኋላም የኤርትራ ህዝብ ያደረገው እንክብካቤ በታሪክ ሊወሳ የሚገባው በጎ ተግባር ነው ፡፡

በከሃዲው ቡድን ላይ የተወሰደው አፀፋዊ እርምጃ ላይ የተሳተፉት የክ/ጦሩ የሰራዊት አባላት ፣ በከፍተኛ እልህና ወኔ ፣ በፍፁም ጀግንነት ያለ አንዳች እረፍት ተልዕኳቸውን እንደተወጡ አብራርተዋል ፡፡

ምንጭ – የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት – ሰለሞን ሁነኛው ( ከግዳጅ ቀጣና ) – ፎቶግራፍ ሽመልስ እሸቱ

Related Post