አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በሃረር ተያዘ

ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በሃረር ተያዘ
ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በሃረር ተያዘ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ87 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ።

በዞኑ ቀርሣ ወረዳ በጊዚያዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በተደረገ ፍተሻ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ በህዝብ ትራንስፖርት በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 87 ሺህ 311 ዶላር በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

የዞኑ ፖሊስ የኮሚዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ቶሎስ ጐሹ በተለይም ለፋና እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪው ህገወጥ ዶላሮቹን በፈሳሽ የህፃናት ወተት ማሸጊያ ውስጥ አስገብቶ አስመስሎ በማሸግ በዳቦ ቅርጫት ውስጥ ካርቶን ሸፍኖበት ሲያጓጉዝ በፀጥታ ሃይሉ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጠርጣሪው ከህገወጥ ዶላሮቹ በተጨማሪ 13 የተለያዩ ባንኮች የሂሳብ ደብተሮች መያዛቸውንም ነው ገልጸዋል።

(ምንጭ – ኢፕድ)

Related Post