አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ከ500 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካዎች መኖራቸው ተነገረ

ከ500 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካዎች መኖራቸው ተነገረ
ከ500 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካዎች መኖራቸው ተነገረ

በአገር አቀፍ ደረጃ ከ500 በላይ ጥቃቅንና አነስተኛ የብረታ ብረት ፋብሪካዎች መኖራቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ግንባታን መርቀው በከፈቱበት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ ሚኒስትሩ መንግስት አገር በቀል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የብርታ ብረት ልማት ለምጣኔ ሃብት ሽግግር ሞተር ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቅሰው፤ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለማስቀረትና ለስራ እድል ፈጠራ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የፋብሪካው ካፒታል 7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን በ5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ማስፋፊያ አድርጎ ተጨማሪ የብረታ ብረትና ቱቦላሬ ምርቶችን ማምረት ጀምሯል። ፋብሪካው በአሁኑ ጊዜ ለ900 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ደግሞ ለ3 ሺህ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

መርሃ ግብሩላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልእክት የኢንዱስትሪ ዘርፍ በመንግስት ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ገልጸዋል። በኢንዱስትሪ ልማት ላይ በተለይም የግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያን ልማት መደገፍ እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

በኢንዱስትሪ ልማት ላይ በተለይም የግሉ ዘርፍ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የኢትዮጵያን ልማት መደገፍ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል። በተለይ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ተፈላጊነት ቀጣይነት ያለው በመሆኑ የግሉ ዘርፍ በስፋት ሊሰማራበት ይገባል ብለዋል።

መንግስት ዘርፉን ለመደገፍ የሚጠበቅበትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደረግ አረጋግጠው፤ ኢትዮጵያዊያን በመደጋገፍ ለአገር ልማት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢንዱስትሪ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ የኢንዱስትሪ ልማትን ለማስፋፋት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በክልል በሺዎች የሚቆጠሩ ከጥቃቅን እስከ ከፍተኛ ያሉ ፕሮጀክቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ወደ ስራ መግባታቸውን ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ የተከፈተው የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ቀደም ሲል ሲያመርታቸው ከነበሩ ሚስማርና ቆርቆሮዎች በተጨማሪ ፌሮዎች፣ የተለያዩ ሽቦዎች እና ሌሎች የብረታ ብረት ውጤቶችን ያመርታል።
(ምንጭ – ኢዜአ)

ተዛማጅ መረጃ

Related Post