አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ከ27.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከ27.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
ከ27.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በዚህ ስድስት ቀናት ውስጥ (ከሰኔ 11-16/12 ዓ.ም) ግምታዊ ዋጋቸው ከ27.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን በመከታተል በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

በሁሉም የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች ላይ ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ ህገወጦችን በመቆጣጠር መንግስት ሊያጣ የነበረ ከ9 ሚሊየን ብር ባለይ ቀረጥና ታክስ እንዲከፈል ተደርጓል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ሳይፈጸም ወደ ሀገር የገቡ ተሸከርካሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ አልባሳት፣ የምግብ ዛይት፣ አደንዛዥ ዕፅና ሺሻ እንዲሁም የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከፌዴራልና ክልሎች ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በተደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ ከነ ኮንትሮባንዲስቶቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

ሁሉንም ተግዳሮቶች ተቋቁሞ የሀገርና የህዝብ ሃብት በመታደግ ላይ የሚገኙ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች፣ ሰራተኞችና የፀረ ኮንትሮባንድ አካላት እንዲሁም ጥቆማ በመስጠት የተባበሩን በሙሉ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምስጋናውን ያቀርባል።

አሁንም የህዝብና የሀገር ሀብት ያላግባብ በኮንትሮባንዲስቶች እንዳይሰረቅ የቁጥጥርና ክትትል ስራችንን አጠናክረን የምንቀጥል በመሆኑ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት የተለመደው ትብብሩን እንዲቀጥል በአክብሮት እንጠይቃለን።

(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post