አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

ከስጋና ወተት ምርት 68 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

ከስጋና ወተት ምርት 68 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
ከስጋና ወተት ምርት 68 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2012 በጀት ዓመት 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የስጋና ወተት ምርት 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒቴር ገለፀ፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ የስጋና ወተት ኢንስቲትዩት የ2012 በጀት ዓመት የ11 ወራት የኤክስፖርት አፈፃፀምን በዘርፉ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከስጋና ወተት 113.81 ሚሊያን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 68.13 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ከበግና ፍየል ስጋ 61.31 ሚሊዮን ዶላር፣ ከዳልጋ ከብት 1.3 ሚሊዮን ዶላር፣ ከእንስሳት ተረፈ ምርት 2.93 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ከማር፣ ከሰም፣ ከዓሳ ምርት እና ከወተት 2.60 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

የእርድ እንስሳት አቅርቦት ጥራት ችግር፣ የእንስሳት ማቆያ እጥረት፣ የብድር አቅርቦት እጥረት፣ ህገ-ወጥ የቁም እንስሳት ንግድና የመብራት መቆራረጥ ምክንያት የተያዘውን እቅድ ሙሉ በሙሉ መፈጸም አልተቻለም ሲሉ የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቱት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ጋሹ ተናግረዋል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው ከሚፈለገው አካል ያለመድረስ እንጅ የአቅርቦት ችግር የለም ያሉ ሲሆን በአቅራቢዎችና በቄራዎች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት እንድኖርና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እንሰራለን በማለት ተናግረዋል፡፡ ዘርፉ አትራፊ ሆኖ አርብቶ አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበት አሰራር በመዘርጋት የኤክስፖርት ስታንዳርድ ዋጋ በማዘጋጀት ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንሰራለን ሲሉም አምባሳደሩ አክለዋል፡፡

(ምንጭ – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሙኒኬሽን)

Related Post