አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

አዲስ አበባ ሲገባ 2500 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ሲገባ 2500 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ ከተማ ሊገባ የነበረ 2500 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ።

ትላንት ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በኤፍ ኤስ አር ጭነት መኪና ተጭኖ ሊገባ የነበረው 2500 የክላሽ ጥይት ኬላ ፍተሻ ላይ መያዙን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ እንዳስታወቁት፤ በፍተሻው ወቅት የጥይቱ አዘዋዋሪና ሹፌሩ ለጊዜው ሲሰወሩ መኪናው እና ጥይቶቹ ቁጥጥር ሥር በመዋል በኤግዚቢትነት ተይዘው በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ሲል የከንቲባ ጽህፈት ቤት የከተማዋን የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል።

(ምንጭ- ኢ.ፕ.ድ)

Related Post