አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች
አንዲት እናት ሦስት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

ወላይታ ዞን ቦዲቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሦስት ወንድ ልጆችን በሰላም ተገላገለች።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ወልዴ ቡቃቶ፤ እናቲት በሆስፒታሉ በቂ የቅድመ ወልድ ህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደቆዩ ገልጸዋል። በዚህም ዛሬ ረፋዱ ሦስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ሦስት ልጆች በሰላም መገላገላቸውን አስታውቀዋል።



ወላዷ እናት በሰላም እንዲገላገሉ የህክምና ባለሙያዎች ላደረጉት ደጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ህፃናቱ የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ ባይሆንም ከሚጠበቀው ክብደት በታች በመሆናቸው ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ልዩ ሆስፒታል ለተሻለ ህክምና መወሰዳቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ የጊዶ ቦዲቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ብርሃነሽ ቆልቻ ከዚህ በፊት የወለዷቸው ሦስት ሴት ልጆች እንዳሏቸውም ለማወቅ ተችሏል።

(ምንጭ – ኢዜአ)

Related Post