አርእስተ ዜና
Tue. Dec 24th, 2024

አርሶ አደሩን የኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማድረግ አስፈላጊ ነው ተባለ

አርሶ አደሩን የኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማድረግ አስፈላጊ ነው ተባለ
አርሶ አደሩን የኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማድረግ አስፈላጊ ነው ተባለ

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትምንትና ምርት ግብይት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ አበበ የግብርና ኢንሹራንስ በአርሶ አደሩ እርሻ ላይ ሊደርስ በሚችለው የተፈጥሮ አደጋ ይበልጥ ተጎጂ እንዳይሆን ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረክታል ብለዋል፡፡ በዚህም ምርትና ምርታማነት እንዲጨምርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ከጃይካ (JICA) ፕሮጅክት ጋር በመተባበር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሩ የሰብል ኢንሹራንስ ተጠቃሚ እንዲሆን ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ይህ ጥረት ውጤት በማምጣቱ ከ12000 በላይ አርሶ አደሮች የጃይካ ኢንሹራንስ ፕሮግራምን መቀላቀላቸው ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳን የጃይካ ፕሮጀክት በተያዘለት ግዜ አምስት ዓመት ሞልቶት ዛሬ ቢያጠናቅቅም ግብርና ሚኒስቴር የተጀመረውን ስራ በሁሉም አከባቢ ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰው ባለፉት ግዜያት በሁሉም ባለድረሻ አካላትና በክልል ባለሙያዎች ተተችቶ በዛሬው እለት ርክክብ የተደረገው መመሪያ ሰነድ በቀጣይ በዚሁ ዙሪያ ለምንሰራው ስራ ተልቅ አስተዋጾ ያበረክታል ብለዋል፡፡

የጃይካ ፕሮጀክት የቡድን መሪ ሱዶ አኪራ በበኩላቸው ባለፉፉት 5 አመታት በግብርና ሚኒስቴርና በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ትብብርና በጃይካ የገንዘብ ድጋፍ 50 ሺህ አርሶ አደሮች የሰብል ኢንሹራንስ ስልጠና ሲወስዱ ከነዚህ ውስጥም ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት አርሶ አደሮች የኢንሹራንሸ ተጠቃሚ መሆናቸውን ግለጸዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ለማ ቦጋለ ባለፉት 5 አመታት ክልሉ ከጃይካ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በተመረጡ 24 ወረዳዎች እና በ133 ቀበሌዎች ላይ የሰብል ኢንሹራንስ ስልጠና ለአርሶ አደሮች የማስተዋወቅ ስልጠና መሰጠቱንና በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት በማድረግ እና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ከኦሮሚያ ኢንሹራንስ ከምፓኒ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ እንዲሁም ለአርሶ አደሩ የኢንሹራንስ ጥቅም ለማስገንዘቢያ የሚሆን መመሪያ ሰነድ ጃይካ ለግብርና ሚኒስቴር በማስረከብ ተጠናቋል፡፡
ምንጭ – የግብርና ሚኒስቴር

Related Post