አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

በሶማሊ ክልል ጎርፍ አደጋ 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ለጉዳት ተዳረጉ

በሶማሊ ክልል ጎርፍ አደጋ 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ለጉዳት ተዳረጉ
በሶማሊ ክልል ጎርፍ አደጋ 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ለጉዳት ተዳረጉ

ከ2012 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ እንዲሁም በባሌ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ በሶማሊ ክልል በዋቢ ሸበሌ፣ፋፋን ዞንና ጅግጅጋ አከባቢ፣በገናሌ እና በዳዋ ወንዞች ላይ ያስከተለው የውሀ ሙላት የፈጠረው ጎርፍ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

የአመቱ መጨረሻ ወራት ላይ አደጋው እያየለ መቶ በሰዎችና በተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የሶማሊ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ሀላፊ አብዱላሂ አብዲ አደን ተናግረዋል። ሀላፊው አክለውም ሲነገሩ በቅርቡ የጣለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ብዙ ሰዎችን ያፈናቀለ ነው ያሉ ሲሆን በቀላፎ፣ በሙስታሂል፣ በፊርፊር፣ጅግጅጋና ፋፋን ዞን አከባቢና በዶልዓዶ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል ብለዋል።

በአደጋው 300ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 200ሺ የሚጠጉት ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ያሉት ሀላፊው በተለይ በሙስታሂል እና በአንዳንድ የቀላፎ ወረዳ አካባቢዎች ውሀው መንደሮችን ከቦ እርዳታ ለመሰድረስ ተቸግረናል ሲሉ ገልፀዋል። በስፍራዎቹ ት/ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የእርሻ ማሳዎች እና የቀበሌና የወረዳ ቢሮዎች ጉዳት ደርሶባቸዋልም ብለዋል።

በአካባቢዎቹ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ ያደረግነው ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ጋር በመተባበር ነው ያሉት ሀላፊው ለእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል በእንቅስቃሴያችን ወቅትም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሰራዊት ላደረገልን ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል። በመጨረሻም በቀጣይ ጊዜያት መሰል ችግር ሊከሰት ስለሚችልም ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሀላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
(ምንጭ – ሶማሊ ኮሙዮኒኬሽን)

Related Post