አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል

በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል

በበጀት ዓመቱ 3ኛ ሩብ ዓመት ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን በአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ሶስተኛ ሩብ ዓመት 2 ሺህ 698 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት አቅዶ 3 ሺህ 5 ፈቃዶችን መስጠቱን ገልጸዋል።
አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ 8 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በአዲስ አበባ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰት አበረታች መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
(ምንጭ-ኢ ፕ ድ)

Related Post