አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

ሲመንስ ጋምሳ በኢትዮጵያ 100 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ሊያመነጭ ነዉ

ሲመንስ ጋምሳ በኢትዮጵያ 100 ሜጋ ዋት የንፋስ ኃይል ሊያመነጭ ነዉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአለም አቀፍ ደረጃ በሃይል አቅርቦት ላይ ከሚሰራው ሲመንስ ጋምሳ ጋር ለ400,000 መኖሪያ ቤቶች የኤሌክትሪክ ብርሃን ማቅረብ የሚያስችል የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት መፈራረሙ ተገለጸ።

የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ በአዳማና አሰላ ከተሞች የሚካሄድ ሲሆን በዓመት እስከ 100 ሜጋ ዋት ሃይል ያመነጫል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። በዓመት እስከ ቶን ወደ አየር የሚለቀቅ ካርቦን እንደሚቀንስ ኩባያዉ ገልፇል። ስምምነቱ የአረንጓዴ ታዳሽ ሃይልን የማስፋፋት አካል መሆኑም ተጠቁሟል።

ሲመንስ ጋምሳ ባወጣው መግለጫ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በሃይል ሴክተሩ ላይ የምታካሂደው የለውጥ እንቅስቀሴና አገሪቱ በታዳሽ ሃይል ላይ ያላትን ሃብት ለመጠቀም የምታካሂደው እንቅስቃሴ አካል መሆኑንም ነው የጠቆመው።

ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ በ2023 መባቻ ላይ ሥራ ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ታውቋል። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 የአገር ውስጥ የሃይል ፍጆታዋን ሙሉ በሙል በታዳሽ ሃይል ለመሸፈን አቅዳ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።
(ምንጭ – ሲመንስ ጋምሳ)

Related Post