አርእስተ ዜና
Fri. Nov 22nd, 2024

ሠራዊቱ ከትግራይ የወጣው አሁን ጁንታው ለአገር አስጊ ባለመሆኑ ነው

ሠራዊቱ ከትግራይ የወጣው አሁን ጁንታው ለአገር አስጊ ባለመሆኑ ነው
ሠራዊቱ ከትግራይ የወጣው አሁን ጁንታው ለአገር አስጊ ባለመሆኑ ነው

ሠራዊቱ ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የተደረገው አሁን ላይ ጁንታው ለአገር አስጊ ባለመሆኑ እና ኢትዮጵያ ካሉባት ችግሮች ውስጥ ቅድሚያ የምትሰጠው ሌላ ጉዳይ በመኖሩ ምክንያት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትላንት ለጋዜጠኞች ምስጋና በተዘጋጀ መርኃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አሸባሪው ህወኃት የማሸነፍ ሳይሆን ሞቶ ሌሎችንም ይዞ መሞት መሆኑን ተናግረዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ከመቐለ እንዲወጣ ሲደረግ ለሳምንት መንግስት በደንብ አስቦበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን መቐለ በወታደራዊ እይታ የስበት ማዕከል አይደለችም ብለዋል።

የአሸባሪው ህወኃት ዓላማ ማሸነፍ ሳይሆን አመድ ሆኛለሁና ተያይዘን አመድ እንሁን የሚል እቅድ መሆኑን ነው የተናገሩት።
መንግስት ባለፉት ወራት ከወታደራዊ ወጭዎች ውጭ ለተለያዩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እና ቀለብ ብቻ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ አድረገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ የክልሉን አጠቃላይ በጀት ስምንት እጥፍ በላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ሆኖ ግን አንድም ዓለም አቀፍ ተቋም እና ሰው ይህንን ጉዳይ ያነሳ የለም ይልቁንም ችግሮቹን ብቻ እየፈለጉ ሲያናፍሱ እንደነበር ነው ያስታወሱት።

በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጀመሪያ ላይ የታጠቀ ሰራዊት ነበር ያጋጠመን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ስናልፍ ደግሞ በሽፍታነት የተደበቀ ሃይል አጋጥሞን የነበረ ቢሆንም ይህንንም በአጭር ጊዜ አጠናቀናል ብለዋል።

አሁን ያለው ሁኔታ የተለየ ሆኖ ሰራዊቱ ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ በሚያደርገው የየእለት ስራ ግን ከጀርባው እየተወጋ መሆኑ ተደጋጋሚ ሆኗል ብለዋል።

ይህ ሁኔታ በወታደሩ ውስጥ መጥፎ ስሜት እየፈጠረ በህዝቡ ላይ ጥቁር ጠባሳ አስቀምጦ እንዳያልፍ እና ለህዝቡም የጥሞና ጊዜ ለመስጠት በማሰብ ነው ሰራዊቱ እንዲወጣ የተደረገው ብለዋል።
(ምንጭ – ኢቢሲ)

Related Post