አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ለ15 የኢትዮጵያ ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው

ለ15 የኢትዮጵያ ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው
ለ15 የኢትዮጵያ ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው

በሁለተኛው የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በስነስርአቱ ላይ የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እንደገለጹት፣ በተለያዩ መመዘኛዎች የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ 15 የኢትዮጵያ ከተሞች ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የወጣባቸውን የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ማሽን ተበርክቶላቸዋል።



ይህ እውቅና ከተማዎች በቀጣይ ጥሩ ስራ እንዲሰሩ ያበረታታል ብለዋል። የኢትዮጵያ የከተሜነት ምጣኔ እየጨመረ መጥቷል ያሉት ሚኒስትሯ፣ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሰራ ቢሆንም አሁንም የመሰረት ልማት፣ የስራ አጥነት፣ የህብረተሰብ አያያዝና መሰል ችግሮች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የከተማ መሰረት ልማት በመንግስት አቅም ብቻ መቅረፍ የማይቻል በመሆኑ ከአበዳሪ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ትልሽከርካሪው የተበረከተላቸው ከተሞችም ደሴ፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ቢሾፍቱ፣ ነቀምቴ፣ ጂማ፣ ጅጅጋ፣ ሀዋሳ፣ቡታጅራ፣ሆሳእና፣ ሰመራ-ሎጊያ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ሀረርና ድሬዳዋ ናቸው።
(ምንጭ – ኢ.ፕ.ድ)


Related Post