በሀገራችን የስራ ፈጣሪዎችና የስራ ፈላጊዎች ቁጥር በጣም የተራራቀ ነዉ። በ2008ዓ.ም ያሬድ እና ጏደኞቿቸው 12 በመሆን እንዲሁም ከNGO በተደረገላቸው ድጋፍ ስራ እንደጀመሩ አቶ አባይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮፒያ ይናገራሉ።
ይህ የማምረቻ ማህበር ለየት የሚያረገው አካል ጉዳተኛን አሰባስቦ የሚሰራ መሆኑ ነው። የህብረት ስራ ማህበሩም ወደፊት የማስፉፉት እቅድ ቢኖራቸውም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ይበልጥ መስራት እንዲችሉ የመንግስት ድጋፍ እንደሚያሻቸው ገልፀዋል።
በአሁኑ ሰአት ሻጮች ከጊዜው ጋር ለመወዳደር በተለያዩ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ምርት ማስተዋወቅ እና መሸጥ ግድ ይላቸዋል። ከዚህ አንፃር አቶ አባይ በማህበራዊ ድህረ ገፆች መሸጥ አለመጀመራቸዉን የአቅም ማነስን እንደ ተግዳሮት ጠቅሰዋል።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ለ3 አመታት የኢትዮጲያ አካልጉዳተኞች እና እድገት ማእከልን በመርዳት ላይ ሲሆን ለ300 አካልጉዳተኞች የሙያ ስልጠናዎችን አቅርቦ 88 ለሚሆኑት ስራ ሲያገኙ ፣ 93 ሚሆኑት የራሳቸውን የቢዝነስ ድርጅት ለመክፈት የሚያስችላቸዉን ድጋፍ ማቅረቡን መረጃዎች ያሳያሉ። መንግስትም እንዲህና መሰል ማበረታቻዎች ላይ ቢሰራ እጅግ ለዉጥ ፈጣሪ ይሆናል።