Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ስለ ተርን ኦቨር ታክስ በጥቂቱ

ስለ ተርን ኦቨር ታክስ በጥቂቱ

ስለ ተርን ኦቨር ታክስ በጥቂቱ

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡

ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ
ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም ዓመታዊ የንግድ አንቅስቃሴው ከብር 1 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ሰብስቦ ለሚመለከተው የታክስ መስሪያ ቤት/ሚኒስቴር ገቢ ያደርጋል፡፡

ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው ወይም ድርጅት በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው ሰብስቦ ለሚስቴሩ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ሻጩ ለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ የስሌት መሠረት
ተርን ኦቨር ታክስ የሚሰላበት የዋጋ መሠረት የዕቃው ወይም የአገልግሎት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ይሆናል፡፡

የሚከተሉት ከተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ነፃ ናቸው፡-
1. ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭና የመኖሪያ ቤት ኪራይ፤
2. የፋይናንሰ አገልግሎቶች፤
3. ለሳንቲሞችና ሜዲሊያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጪ አገር ገንዘቦችና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት፤
4. በኃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች፤

5. የሕክምና አገልግሎትና አግባብ ባለው የመንግስት መ/ቤት በሚወጣ መመሪያ መሠረት በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፤
6. በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋዕለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች፤
7. የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲን የውሃ አቅርቦት፤

8. የትራንስፖርት አገልግሎት፤
9. ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚሰጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚፈፀም ክፍያ፤
10. 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
11. መጽሐፍት፤
12. ሌሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ ሁሉ ናቸው፡፡

(ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር)

Exit mobile version