ስለድርጅታችን

ድርጅትዎን በነጻ በማስተዋወቅ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ይጠቀሙ

ኢትዮጵያ በቅርቡ የተቀላቀለችዉን የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመደገፍ በሃቅ መልቲሚድያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሱና ህጋዊ ምዝገባ ላደረጉ የግል ድርጅቶች በሙሉ ምርትና አገልግሎቶቻቸዉን በኢንተርኔት (በበይነመረብ) ላይ ያለምንም ክፍያ እንዲያስተዋዉቁ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እድል አመቻችቷል።

ስለዚህም በዚህ የበሃቅ መልቲሚድያ የኢትዮጵያ ቢዝነስ ዳይረክተሪ ላይ ድርጅትዎን እንዲያስመዘግቡ እንጋብዝዎታለን። ይህም ሰዎች እርስዎ በተሰማሩበት የቢዝነስ ዘርፍ ስለአንድ ምርት ወይም አገልግሎት በይነመረብ ላይ በሚፈልጉበት ጊዜ (ጉግል ሲያደርጉ) የእርስዎን ድርጅት በቀላሉ ለማግኘት ይረዳቸዋል።

በሃቅ መልቲሚድያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በኢትዮጵያ የተመዘገበና፤ ላለፉት 13 አመታት (ከህዳር 2002 ጀምሮ) የቢዝነስና የኢኮኖሚ ዜናዎችን በእንግሊዝኛ ቋንቋ እያሰራጨ የሚገኘዉን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ የተባለዉን የበይነመረብ የመረጃ ማሰራጫ የሚያስተዳደር ተቋም ነው።

ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የተመዘገበ ሲሆን፤ በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክርቤት አባል ነው።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ሆነ፤ ተዛማጅ የሚድያና የህዝብ ግንኙነት አገልግሎቶችን ከፈለጉ ይደዉሉልን ወይም ወደ ቢሯችን ብቅ ይበሉ።

ድርግትዎን በነጻ ለማስመዝገብ መረጃዎን በኢሜል ወይም በአጭር መልእክት (SMS) በስልክ ይላኩልን።
ስልክ +251118932529 / +251911407539 info (@) newbusinessethiopia.com