Site icon ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ

ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አንዳንድ መረጃዎች

ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አንዳንድ መረጃዎች

ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አንዳንድ መረጃዎች

ስለሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ (sales register machine) አንዳንድ መረጃዎች

1. የመሳሪያው አቅራቢ መሳሪያውን ከውጪ ማስገባትና አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት እውቅና ከሚኒስቴሩ ሊያገኝ ይገባል፡፡
2. መሳሪያው ብልሽት ቢያጋጥመውና ተጠቃሚው የመሳሪያውን እሽግ ሳይሰብር ሊያስተካክለው የማይችል ከሆነ በመሳሪያው መጠቀሙን ወዲያውኑ አቋርጦ ብልሽቱ ያጋጠመበትን ጊዜ በምርመራ መዝገቡ ላይ መመዝገብና በ2 ሰአት ውስጥ ለሚኒስቴሩ ለአገልግሎት ማእከሉ በስልክ ማስታወቅ አለበት፡፡

3. የተበላሸው መሳሪያ እስከሚስተካከል ወይም በሌላ መሳሪያ እስከሚተካ ተጠቃሚው በሚኒስቴሩ ፈቃድ በታተመ ደረሰኝ ግብይቱን ማከናወን አለበት፡፡ ሆኖም በታተመ ደረሰኝ ግብይት ማከናወን የሚችለው በአንድ አመት ውስጥ ከ5 ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡

4. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያው የባለቤትነት መብት ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት የተላለፈ እንደሆነ ቀደም ሲል የመሳሪያው ባለቤት የነበረው ሰው ወይም ድርጅት ይጠቀምበት የነበረው የፊሲካል ማስታወሻ ከመሳሪያው እንዲወጣ ተደርጎ በአዲስ ይተካል፡፡

5. የባለቤትነት ለውጥ ሲደረግ መሳሪያውን የገዛው ሰው ከተመዘገበ የአገልግሎት ማዕከል ጋር ውለታ መግባት ያለበት ሲሆን መሳሪያውን መጀመሪያ ይጠቀምበት ለነበረው ተጠቃሚ የሸጠው የመሳሪያ አቅራቢ ይህንኑ ለውጥ ለሚኒስቴሩ በ5 ቀን ውስጥ ማስታወቅ ይገባዋል፡፡ አዲሱ ተጠቃሚም መሳሪያውን በሚኒስቴሩ ዘንድ ማስመዝገብ አለበት፡፡

(ምንጭ የገቢዎች ሚኒስቴር)

Exit mobile version